Blog
ቤርያን ልረሳ አልቻልኩም
ታሪካዊቷን የዳላስ ከተማ ስናስብ ዓለምን ያሳዘነውንና ያስደነገጠውን የአሜሪካ ፕሬዝዳንት የነበሩት ጆን ኤፍ ኬኔዲ ግድያ አለማሰብ አይቻልም:: በዚህች ከተማ በቆየሁበት ጥቂት ቀናቶች ይህን ታሪካዊ ቦታ (Dealey Plaza) የመመልከት እድሉ ገጥሞኛል::
አንድም በዚህች ከተማ አግራሞት ከጫሩብኝ ቦታዎች መካከል (Reunion Tower) ካልተሳሳትኩኝ በትርጉም የመሰብሰቢያ ግንብ ተብሎ የሚጠራው ሲሆን የዳላስ ከተማን ውበት ከከፍታ ለማየት እረድቶኛል:: ወደዚች ከተማ የምትመጡ እነዚህን ቦታዎች እንድትመለከቱም ወንድማዊ ምክሬ ነው::
በተጨማሪ ይህን ቆይታዬን የተሳካ እንዲሆን የተራዳችሁኝን ሁላችሁንም አንድም በይበልጥ ወንድሜን ናሙና ጌታሁን አመሰግናለሁ::
በመጨረሻ እንኳን ለታላቁ የዐቢይ ጾም አደረሳችሁ አደረሰን እያልኩኝ አንድ የማልክደው እውነት አለ እርሱም ምንም በስጋ ዳላስ ቴክሳስ ብሆንም ልቤ ግን ያለው ከቤርያ (ሐዋ 17) ምዕመናን ጋር ነው:: ስለዚህ የሐዋርያት ሥራ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ሰኞ በኢትዮጵያ የሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 1 ሰዓት ላይ ይቀጥላል::
“ብቻውን ጥበብ ላለው ለእግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ እስከ ዘላለም ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን።” ወደ ሮሜ ሰዎች 16:27
Photographer: Namuna Kassaye
ዲያቆን ዘአማኑኤል ተስፋዬ
ዳላስ ቴክሳስ
March, 10/2024